አዛውንቶች (65+)
ዕድሜያቸው ከ 65 ዓመት በላይ ሆኗቸው ከአቻዎቻቸው ጋር ጓደኝነትን ለሚፈልጉ እና ቀለል ያለ አካላዊ እንቅስቃሴ የሚፈልጉትን ለቀን እንቀበላለን። የምንቀበላቸው አዛውንቶች ያለምንም ድጋፍ በራሳቸው የሚነቀሳቀሱም ቢሆኑ ወይም ለመመገብ እና ለመንቀሳቀስ ድጋፍ ቢያስፈልጋቸው፥ የተቋማችን ሰራተኞች አስፈላጊውን ለማድረግ የተዘጋጁ ናቸው።
ጎልደን ይርስ ቲ. ፒ.ኤል.ሲ — የአዋቂዎች ቀን እንክብካቤ ማዕከል
ማዕከላችን ለአዛውንቶች በቀን ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ከአቻዎቻቸው የሚገናኙበት እና ቀናቸውን የሚያሳልፉበት ስፍራ ሲሆን ለቤተሰቦቻቸውና ለተንከባካቢዎቻቸው ደግሞ እምነት የሚጥሉበትና የቀን ድጋፍ የሚያገኙበት ነው። ማዕከላችን ዕድሜያቸው ከ65 ዓመት በላይ ለሆኑ አዛውንቶች እና ከዚያ ባነሰ ዕድሜ ላይ ሆነው ከማስታወስ ጋር በተያያዘ ሁኔታ ውስጥ ሆነው እንክብካቤ የሚያስፈልጋቸውን በርህራሄና በፍቅር እንክብካቤ ማድረግ ልዩ ተሰጥኦችን ነው።
እንክብካቤ - በአክብሮ! አገልግሎት - ከልብ!
ጎልደን ይርስ የአዛውንቶች እንክብካቤ ማዕከል የተቋቋመው፥ ሰዎች ከሚወዷቸው ጋር አብረው በመሆን ለመንከባከብ በማይችሉበት ጊዜ ሃሳባቸውን የሚጥሉበት ተንከባካቢ ለመሆን ነው። ለሚወዷቸው ደህንነቱ የተጠበቀ፥ ተነቃቅተው የሚውሉበት እና በአክብሮት የሚያዙበት ሁኔታ እንዲኖር ለሚፈልጉ ነው።። እኛ የተደራጀ የቀን የውሎ ፕሮግራምን ከሞቀ አቀባበልና ከፍተኛ የሙያ ስነምግባር ጋር ስንጠብቅዎና፥ የምንንከባከባቸው ትርጉም ባለው ማኅበራዊ ሕይወት ውስጥ ሲያሳልፉ፥ እርስዎ ሥራዎ ላይ ወይም ጉዳይዎ ላይ ማተኮር እንዲችሉ ነው። የተቋማችን ሰራተኞች የኢትዮጵያውያንን የቤተሰብ እሴቶች ይገነዘባሉ፤ በመሆኑም እያንዳንዱ ቀን ከምቾት ፥ ከባህል እና ከአክብሮት አኳያ የተቃኘ ነው።
ስለ ተልዕኳችን ይወቁማዕከላችን ሲደራጅ በዚያው እየኖሩ አገልግሎት የሚያገኙበት ሳይሆን የቀን እንክብካቤ የሚያስፈልጋቸውን አዛውንቶች ታሳቢ በማድረግ ነው በመሆኑ አዛውንቶች ልዩ ቀን እንዲያሳልፉ ያልተቋረጠ ሙያዊ ክትትል ይደረግበታል።
ዕድሜያቸው ከ 65 ዓመት በላይ ሆኗቸው ከአቻዎቻቸው ጋር ጓደኝነትን ለሚፈልጉ እና ቀለል ያለ አካላዊ እንቅስቃሴ የሚፈልጉትን ለቀን እንቀበላለን። የምንቀበላቸው አዛውንቶች ያለምንም ድጋፍ በራሳቸው የሚነቀሳቀሱም ቢሆኑ ወይም ለመመገብ እና ለመንቀሳቀስ ድጋፍ ቢያስፈልጋቸው፥ የተቋማችን ሰራተኞች አስፈላጊውን ለማድረግ የተዘጋጁ ናቸው።
ከመርሳት ጋር የተያያዘ ሁኔታ ውስጥ ያሉ በማዕከላችን የተደራጀ እና በልምድ የታገዘ ድጋፍ ያገኛሉ። በወጥነት በሚኖሩ ፕሮግራሞች፥ ለማስታወስ በሚያግዙ ክፍሎች፥ እየተመሩ በሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎች ጭንቀት እንዲቀንሱና የማስታወስ አቅማቸው እንዲዳብር ይታገዛሉ። - ሁሉም በትዕግስት ከአክብሮት ጋር።
የእንክብካቤ ማዕከላችን ለአዛውንቶች ብቻ ሳይሆን ለተንከባካቢ ቤተሰቦችም ነው። ሥራን፥ ቤተሰባዊ ግዴታዎችን፥ እና የመንከባከብ ሃላፊነትን አመጣጥኖ በመምራት ውስት ላለ ድካም እና ጫና፥ ጎልደን ይርስ አስተማማኝ የቀን እንክብካቤ በመስጠት፥ ለእርስዎ አካላዊና አእምሯዊ እረፍትን ያቀረበ ማዕከል ነው። በዚህም የሚወዷቸው በደህና እንዳሉ፥ በሰዓታቸው በአግባቡ እየተመገቡ እንዳሉና ማኅበራዊ ግንኙነታቸው በጥሩ ሁኔታ ላይ እንዳሉ ሊያዩ ይችላሉ።
እያንዳንዱ ቀን በጥንቃቄ ይዘጋጃል፡ ጠዋት ሞቅ ያለ አቀባበል ጋር ቀላል የአካል እንቅስቃሴ፣ የሚያውቁት ምግብ፣ ከሌሎች ጋር የሚገናኙበት እና አእምሮን ዘና የሚያደርጉ ጨዋታዎች ሰላማዊ የእረፍት ጊዜ እና ከሰዓት በኋላ ወደቤት ከመሄዳቸው በፊት አሳታፊ እና አነቃቂ ፕሮግራም ይኖራቸዋል። ፕሮግራሞቹን የቀረጽነው በጣም ሳይደክሙብን ብርታትን ተሞልተው እንዲውሉ ሲሆን፣ ቤተሰቦች ደግሞ ግልጽ የውሎ መረጃ ይሰማሉ።
ዕለታዊ ፕሮግራም ይመልከቱየእኛን የቀን እንክብካቤ ልዩ ያደረገው ምንድነው ነው?
እያንዳንዱ ፖሊሲ፣ ቦታና ፕሮግራም ለ65+ እና ለማህደር ፍላጎት ብቻ ተዘጋጅቷል — አጠቃላይ ተቋም ሳይሆን የቀን እንክብካቤ ማዕከል።
ማዕከላችን የታወቁ እንቅስቃሴዎች የሚደረጉበት፣ የሰለጠኑ ተቆጣጣሪዎች ያሉበት፥ ደህንነቱ የተጠበቀ ሥፍራ መሆኑ እና ለማድረስና መልሶ ለመውሰድ አማካይ ቦታ ላይ መገኘቱ ለቤተሰቦች የልብ መተማመንን ይፈጥራል።
ከምግብ እስከ በዓላት አከባበር — የኢትዮጵያውያንን ባህል ባከበረ መልኩ እናካሂዳለን፣ የምንንከባከባቸውም ከቤት ውጭ እንዳሉ ሳይሆን በቤታቸው እንዳሉ ይሰማቸዋል።